ማሕልየ መሓልይ 6:1-3
ማሕልየ መሓልይ 6:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ልጅ ወንድምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወንድምሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ? ልጅ ወንድሜ በገነቱ መንጋውን ይጠብቅ ዘንድ፥ አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ። እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ ልጅ ወንድሜም የእኔ ነው፤ በሱፍ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።
ማሕልየ መሓልይ 6:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? ዐብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣ የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ ወደ አትክልት ቦታው ወርዷል። እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው፤ መንጋውንም በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።
ማሕልየ መሓልይ 6:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ውድሽ ወዴት ሄደ? ውድሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ? ውዴ በገነቱ መንጋውን ያሰማራ ዘንድ አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ። እኔ የወዴ ነኝ ውዴም የእኔ ነው፥ በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።