መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 6:1-3

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 6:1-3 አማ2000

አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከአ​ንቺ ጋር እን​ፈ​ል​ገው ዘንድ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወን​ድ​ም​ሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ? ልጅ ወን​ድሜ በገ​ነቱ መን​ጋ​ውን ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ አበ​ባ​ው​ንም ይሰ​በ​ስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ። እኔ የልጅ ወን​ድሜ ነኝ፥ ልጅ ወን​ድ​ሜም የእኔ ነው፤ በሱፍ አበባ መካ​ከል መን​ጋ​ውን ያሰ​ማ​ራል።