የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መኃልየ መኃልይ 6

6
1አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥
ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ውድሽ ወዴት ሄደ?
ውድሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?
2ውዴ በገነቱ መንጋውን ያሰማራ ዘንድ
አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ
ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።
3እኔ የወዴ ነኝ ውዴም የእኔ ነው፥
በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።
4ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥
እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፥
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።
5አውከውኛልና ዓይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፥
ጠጕርሽ ከገለዓድ እንደ ወረደ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
6ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ
ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
7በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
8ስድሳ ንግሥታት ሰማንያም ቍባቶች
ቍጥር የሌላቸውም ቈነጃጅት አሉ።
9ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፥
ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት።
ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥
ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት።
10ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥
እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
11የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥
ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እመለከት ዘንድ
ወደ ገውዝ ገነት ወረድሁ።
12ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሰረገላ ላይ አስቀመጠችኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ