መኃልየ መኃልይ 6:1-3

መኃልየ መኃልይ 6:1-3 አማ05

አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ! ወዳጅሽ ወዴት ሄደ? እኛም አብረንሽ እንድንፈልገው የሄደበትን አቅጣጫ ንገሪን። ውዴ የበጎቹን መንጋ ለማሰማራትና ውብ አበባን ለመቅጠፍ፥ የሽቶ ዕፀዋት ወደሚገኙበት የአትክልት ቦታው ወርዶአል። ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።