ራእይ 4:8-11
ራእይ 4:8-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም። እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤” ክብር ውዳሴ ኃይልም እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
ራእይ 4:8-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች ነበሯቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸው በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ፤ ቀንና ሌሊትም፦ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ” ማለትን አያቋርጡም። ሕያዋን ፍጡራኑ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ክብር፣ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ይሰግዱ ነበር፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው እንዲህ ይላሉ፤ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና።”
ራእይ 4:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም። እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
ራእይ 4:8-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች ነበሩአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ሌሊትና ቀን፦ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፥ የነበረ፥ ያለና የሚመጣውም” ከማለት አያቋርጡም ነበር። እንስሶቹ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለሚኖረው ገናናነት፥ ክብርና ምስጋና በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ፥ ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ ሁሉን ነገር ስለ ፈጠርክ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የሚኖረው (ሕይወትን ያገኘው) በአንተ ፈቃድ ስለ ሆነ ገናናነት፥ ክብርና ኀይልም ለአንተ ይገባል” ይሉ ነበር።
ራእይ 4:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር። እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ገናናነት ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ይሰግዳሉ፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው እንዲህ ይላሉ፥ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ገናናነት ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል፤”