የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ራእይ 4

4
የእግዚአብሔር ዙፋንና ሰማያዊው የጸሎት ሥነ ሥርዓት
1ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ! እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበትን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ። 2#ሕዝ. 1፥26-28፤ 10፥1።ወዲያው በመንፈስ ተመሰጥሁ፤ እነሆም ዙፋን በሰማይ ተዘጋጀ፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበረ፤ 3ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ። 4በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር። 5#ዘፀ. 19፥16፤ ጦቢ. 12፥15፤ ራእ. 8፥5፤ 11፥19፤ 16፥18፤ ሕዝ. 1፥13፤ ራእ. 1፥4፤ ዘካ. 4፥2።ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት ችቦዎች ይቀጣጠሉ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። 6#ሕዝ. 1፥22።#ሕዝ. 1፥5-10፤ 10፥14።በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ። 7ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበር ንስር ይመስል ነበር። 8#ሕዝ. 1፥18፤ 10፥12፤ ኢሳ. 6፥2፤3።አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤
“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም
ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ”
ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር። 9እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ገናናነት ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥ 10ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ይሰግዳሉ፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው እንዲህ ይላሉ፥
11“ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና
ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና
ክብር ገናናነት ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል፤”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ