መዝሙር 95:3-7
መዝሙር 95:3-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ክብሩን ለአሕዛብ፥ ተአምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ፤ እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዝአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ። እምነትና በጎነት በፊቱ፥ ቅድስናና የክብር ገናናነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። የአሕዛብ ወገኖች፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፤
ያጋሩ
መዝሙር 95 ያንብቡመዝሙር 95:3-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው። የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የርሱ ናቸው። እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ። ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣ የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።
ያጋሩ
መዝሙር 95 ያንብቡ