መጽሐፈ መዝሙር 95:3-7

መጽሐፈ መዝሙር 95:3-7 አማ05

እግዚአብሔር ታላቅ ንጉሥ ነው፤ በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይም ንጉሥ ነው። የመሬት ጥልቀቶች በመዳፉ ውስጥ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው። እርሱ የፈጠረው ስለ ሆነ ባሕር የእርሱ ነው፤ የብስንም የፈጠሩ እጆቹ ናቸው። ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ! እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤