መጽሐፈ መዝሙር 95
95
የምስጋና መዝሙር
1ኑ፤ እግዚአብሔርን በመዝሙር እናመስግን!
ለመዳናችን አምባም የድል እልልታ እናስተጋባለት!
2ወደ ፊቱ ቀርበን እናመስግነው፤
በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል!
3እግዚአብሔር ታላቅ ንጉሥ ነው፤
በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይም ንጉሥ ነው።
4የመሬት ጥልቀቶች በመዳፉ ውስጥ ናቸው፤
የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።
5እርሱ የፈጠረው ስለ ሆነ ባሕር የእርሱ ነው፤
የብስንም የፈጠሩ እጆቹ ናቸው።
6ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ!
በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!
7እርሱ አምላካችን ነው፤
እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤
ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦
8“በዚያ በበረሓ ቦታ፥ በመሪባና በማሳ
የቀድሞ አባቶቻችሁ እንዳደረጉት እልኸኞች አትሁኑ። #ዕብ. 3፥15፤ 4፥7።
9እነርሱ ያደረግኹላቸውን ድንቅ ነገር ቢያዩም እንኳ
በዚያ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም። #ዘፀ. 17፥1-7፤ ዘኍ. 20፥2-13።
10ያን ሕዝብ አርባ ዓመት ሙሉ ተጸየፍኩት፤
‘እነርሱም ልባቸው የባከነና
እኔን መከተል ያላወቁ ሰዎች ናቸው’ አልኩ።
11ተቈጥቼም ‘ዕረፍት ወደምታገኙባት ምድር
ከቶ አትገቡም’ ብዬ ማልኩ።” #ዕብ. 3፥7-11። #ዘኍ. 14፥20-23፤ ዘዳ. 1፥34-36፤ 12፥9-10፤ ዕብ. 4፥3-5።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 95: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997