መጽሐፈ መዝሙር 96
96
እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ መሆኑ
(1ዜ.መ. 16፥23-33)
1ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ!
በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ!
2ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ አመስግኑትም!
የአዳኝነቱን መልካም ዜና በየቀኑ አብሥሩ!
3በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤
ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ!
4እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤
ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤
ከአማልክትም ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል።
5ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።
6በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤
ኀይልና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።
7በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ!
ስለ ክብሩና ስለ ኀይሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
8ለስሙ ተገቢ የሆነውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ወደ መቅደሱም አደባባይ መባ ይዛችሁ ቅረቡ።
9ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ!
የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ!
10በሕዝቦች መካከል “እግዚአብሔር ንጉሥ ነው!
ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፤
እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ በትክክል ይፈርዳል” በሉ።
11ሰማይና ምድር ደስ ይበላቸው!
ባሕርና በውስጡ ያሉት ሁሉ እልል ይበሉ!
12ማሳና በላይዋ የሚገኙ ሰብሎች ሁሉ ደስ ይበላቸው!
ከዚያም የደን ዛፎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደስታ ይዘምሩ፤
13እርሱም በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሰዎች ላይ በእውነተኛነቱ ይፈርዳል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 96: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997