መዝሙር 63:3-6
መዝሙር 63:3-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንደ እባብ ምላሳቸውን አሰሉ፤ መራራ ነገርን ለማድረግ፥ ንጹሕንም በስውር ለመግደል ቀስትን ገተሩ፤ በድንገት ይነድፏቸዋል አይፈሩምም። ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ የሚያምንም የለም ይላሉ። ዐመፃን ፈለጓት፥ ሲፈትኑም ሲጀምሩም አለቁ፤ ሰው በጥልቅ ልብ ውስጥ ይገባል፥
ያጋሩ
መዝሙር 63 ያንብቡመዝሙር 63:3-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል። በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 63 ያንብቡመዝሙር 63:3-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ። ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ። በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 63 ያንብቡ