መዝ​ሙረ ዳዊት 63:3-6

መዝ​ሙረ ዳዊት 63:3-6 አማ2000

እንደ እባብ ምላ​ሳ​ቸ​ውን አሰሉ፤ መራራ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ፥ ንጹ​ሕ​ንም በስ​ውር ለመ​ግ​ደል ቀስ​ትን ገተሩ፤ በድ​ን​ገት ይነ​ድ​ፏ​ቸ​ዋል አይ​ፈ​ሩ​ምም። ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ክፉ ነገ​ርን አጸኑ፤ ወጥ​መ​ድን ይሰ​ውሩ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ የሚ​ያ​ም​ንም የለም ይላሉ። ዐመ​ፃን ፈለ​ጓት፥ ሲፈ​ት​ኑም ሲጀ​ም​ሩም አለቁ፤ ሰው በጥ​ልቅ ልብ ውስጥ ይገ​ባል፥