መዝሙረ ዳዊት 63
63
1 #
1ሳሙ. 24። በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 42፥2፤ 143፥6፤ ኢሳ. 26፥9። አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥
ነፍሴ አንተን ተጠማች፥
ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች
በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
3ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ
እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
4ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና
ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
5እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥
በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
6ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥
ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።
7በመኝታዬም አስብሃለሁ፥
በማለዳም ስለ አንተ አሰላስላለሁ፥
8 #
መዝ. 17፥8፤ 36፥8። ረዳቴ ሆነኸኛልና፥
በክንፎችህም ጥላ በደስታ እዘምራለሁ።
9ነፍሴ ከኋላህ ተቆራኘች፥
እኔንም ቀኝህ#63፥9 ቀኝ እጅህ ተቀበለችኝ።
10እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት፥
ወደ ምድር ጥልቅ ይገባሉ።
11ለሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጣሉ፥
የቀበሮም እድል ፈንታ ይሆናሉ።
12 #
መዝ. 107፥42። ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥
በእርሱ የሚምል ሁሉ ይከብራል፥
ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 63: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ