የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 63

63
መዝሙር 63
እግዚአብሔርን መፈለግ
በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤
አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣
በደረቅና በተራቈተ ምድር፣
ነፍሴ አንተን ተጠማች፤
ሥጋዬም አንተን ናፈቀች።
2ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤
ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።
3ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤
ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
4እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤
በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
5ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤
አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
6በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤
ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።
7አንተ ረዳቴ ነህና፣
በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።
8ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤
ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።
9ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣
ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤
10ለሰይፍ ዐልፈው ይሰጣሉ፤
የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።
11ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤
በእግዚአብሔርም ስም ቃል የሚገቡ ሁሉ ይከብራሉ፤
የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች።

Currently Selected:

መዝሙር 63: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ