የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 34:11-22

መዝሙር 34:11-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ። ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለ​ሱ​ልኝ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ልጆ​ችን አሳ​ጡ​አት። እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥ ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤ ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ። ለወ​ዳ​ጆቼና ለወ​ን​ድ​ሞቼ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አደ​ረ​ግሁ፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና እን​ደ​ሚ​ተ​ክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደ​ረ​ግሁ። በእኔ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ፥ ደስም አላ​ቸው፤ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ ተማ​ከሩ፥ እኔ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም። ተሰ​በሩ፥ አል​ደ​ነ​ገ​ጡ​ምም። ፈተ​ኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበ​ቱ​ብኝ፥ ሣቁ​ብ​ኝም፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አን​ቀ​ጫ​ቀጩ። አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ? ነፍ​ሴን ከክፉ ሥራ​ቸው፥ ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አድ​ናት፥ አቤቱ፥ በታ​ላቁ ጉባኤ ውስጥ እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፥ በብዙ ሕዝብ መካ​ከ​ልም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም። ለእ​ኔስ ሰላ​ምን ይና​ገ​ሩ​ኛ​ልና፥ በግ​ር​ፋ​ትም ያጠ​ፉኝ ዘንድ ይመ​ክ​ራሉ። አፋ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አላ​ቀቁ፤ እሰይ፥ እሰይ፥ በዐ​ይ​ና​ችን አየ​ነው ይላሉ። አቤቱ፥ አንተ እይ፥ ዝምም አት​በል፤ አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ።

መዝሙር 34:11-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ። ሕይወትን የሚወድድ፣ በጎውንም ያይ ዘንድ ዕድሜን የሚመኝ ማን ነው? አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ። ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም። የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው። የእግዚአብሔር ፊት ግን፣ መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው። ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል። የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል። ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል። እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤ እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።

መዝሙር 34:11-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ። ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው? እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ። ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም። እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል። ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል። ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል። ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም። ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤ ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ። እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤ በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።