የዐመፃ ምስክሮች ተነሡብኝ፥ የማላውቀንም በእኔ ላይ ተናገሩ። ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለሱልኝ፥ ሰውነቴንም ልጆችን አሳጡአት። እኔስ ባሠቃዩኝ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፤ ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ። ለወዳጆቼና ለወንድሞቼ እንደማደርግ አደረግሁ፤ እንደሚያለቅስና እንደሚተክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ። በእኔ ላይ ተሰበሰቡ፥ ደስም አላቸው፤ ይገርፉኝ ዘንድ ተማከሩ፥ እኔ ግን አላወቅሁም። ተሰበሩ፥ አልደነገጡምም። ፈተኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበቱብኝ፥ ሣቁብኝም፤ ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ። አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈርድልኛለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፥ ብቸኝነቴንም ከአንበሶች አድናት፥ አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለሁ፥ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ። በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጠሉኝና በዐይናቸው የሚጠቃቀሱብኝም። ለእኔስ ሰላምን ይናገሩኛልና፥ በግርፋትም ያጠፉኝ ዘንድ ይመክራሉ። አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፤ እሰይ፥ እሰይ፥ በዐይናችን አየነው ይላሉ። አቤቱ፥ አንተ እይ፥ ዝምም አትበል፤ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።
መዝሙረ ዳዊት 34 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 34:11-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos