የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 34

34
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ የሚ​በ​ድ​ሉ​ኝን በድ​ላ​ቸው፥
የሚ​ዋ​ጉ​ኝ​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።
2ጋሻና ጦር ያዝ፥
እኔ​ንም ለመ​ር​ዳት ተነሥ።
3ሰይ​ፍ​ህን ምዘዝ፥ የሚ​ከ​ብ​ቡ​ኝ​ንም ክበ​ባ​ቸው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝን ክበ​ባ​ቸው” ይላል።
ነፍ​ሴን፦ ረዳ​ትሽ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መድ​ኀ​ኒ​ትሽ” ይላል። እኔ ነኝ በላት።
4ነፍ​ሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐ​ሳ​ቈ​ሉም፤
ክፋ​ትን በእኔ ላይ የሚ​መ​ክሩ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚ​ያ​ስቡ” ይላል። ይፈሩ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ።
5በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ትቢያ ይሁኑ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው።
6መን​ገ​ዳ​ቸው ዳጥና ጨለማ ትሁን፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያሳ​ድ​ዳ​ቸው።
7በከ​ንቱ ያጠ​ፉኝ ዘንድ ወጥ​መ​ዳ​ቸ​ውን ሸሽ​ገ​ው​ብ​ኛ​ልና፥
ነፍ​ሴን በከ​ንቱ አበ​ሳ​ጭ​ተ​ዋ​ታ​ልና።
8ያላ​ወ​ቋት ወጥ​መድ ትም​ጣ​ባ​ቸው፥
የሸ​ሸ​ጓ​ትም ወጥ​መድ ትያ​ዛ​ቸው፤
በዚ​ህ​ችም ወጥ​መድ ውስጥ ይው​ደቁ።
9ነፍሴ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይላ​ታል፥
በማ​ዳ​ኑም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች።
10አጥ​ን​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይሉ​ሃል፦
“አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?
ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ
ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ከሚ​ነ​ጥ​ቀው እጅ ታድ​ነ​ዋ​ለህ።”
11የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥
የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የማ​ላ​ው​ቀ​ውን ጠየ​ቁኝ” ይላል።
12ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለ​ሱ​ልኝ፥
ሰው​ነ​ቴ​ንም ልጆ​ችን አሳ​ጡ​አት።
13እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥
ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤
ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ።
14ለወ​ዳ​ጆቼና ለወ​ን​ድ​ሞቼ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አደ​ረ​ግሁ፤
እን​ደ​ሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና እን​ደ​ሚ​ተ​ክዝ
ራሴን ዝቅ ዝቅ አደ​ረ​ግሁ።
15በእኔ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ፥ ደስም አላ​ቸው፤
ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ ተማ​ከሩ፥ እኔ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም።
ተሰ​በሩ፥ አል​ደ​ነ​ገ​ጡ​ምም።
16ፈተ​ኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበ​ቱ​ብኝ፥ ሣቁ​ብ​ኝም፤#“ሣቁ​ብኝ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አን​ቀ​ጫ​ቀጩ።
17አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ?
ነፍ​ሴን ከክፉ ሥራ​ቸው፥
ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አድ​ናት፥
18አቤቱ፥ በታ​ላቁ ጉባኤ ውስጥ እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ” ይላል።
በብዙ ሕዝብ መካ​ከ​ልም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
19በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥
በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።#ዕብ. “አይ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብኝ” ይላል።
20ለእ​ኔስ ሰላ​ምን ይና​ገ​ሩ​ኛ​ልና፥
በግ​ር​ፋ​ትም ያጠ​ፉኝ ዘንድ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በቍ​ጣም ሺን​ገ​ላን ይመ​ክ​ራሉ” ይላል። ይመ​ክ​ራሉ።
21አፋ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አላ​ቀቁ፤
እሰይ፥ እሰይ፥ በዐ​ይ​ና​ችን አየ​ነው ይላሉ።
22አቤቱ፥ አንተ እይ፥ ዝምም አት​በል፤
አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ።
23አቤቱ ተነሥ፥ ፍር​ዴ​ንም አድ​ምጥ፥
አም​ላኬ ጌታ​ዬም፥ በክ​ር​ክሬ ጊዜ ተነሥ፥
24አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፥
በእ​ኔም ላይ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው።
25በል​ባ​ቸ​ውም በሰ​ው​ነቴ ላይ፥ “እሰይ እሰይ፥” አይ​በሉ፤
“ዋጥ​ነ​ውም” አይ​በሉ።
26በመ​ከ​ራዬ ደስ የሚ​ላ​ቸው ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፤
በእኔ ላይ ነገ​ርን የሚ​ያ​በዙ እፍ​ረ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን ይል​በሱ።
27ጽድ​ቄን የሚ​ወ​ድ​ዱ​አት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥
ሐሤ​ት​ንም ያድ​ርጉ፤
የባ​ሪ​ያ​ህን ሰላም የሚ​ወዱ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁል​ጊዜ ታላቅ ነው ይበሉ።
28ምላሴ ጽድ​ቅ​ህን፥
ሁል​ጊ​ዜም ምስ​ጋ​ና​ህን ይና​ገ​ራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ