ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ። ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው? እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ። ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም። እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል። ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል። ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል። ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም። ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤ ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ። እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤ በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።
መጽሐፈ መዝሙር 34 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 34:11-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos