የአንበሳ ደቦሎች ተቸገሩ፥ ተራቡም፥ ጌታን የሚፈልጉት ግን መልካሙን ሁሉ አያጡም። ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፥ ጌታን መፍራት አስተምራችኋለሁ። ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ? አንደበትህን ከክፉ ነገር፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን ከመናገር ከልክል። ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም። የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና። መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የጌታ ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ተነሥቶአል። ጻድቃን ጮኹ፥ ጌታም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው። ጌታ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል። የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ ጌታ ግን ከሁሉ ያድናቸዋል። አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።
መዝሙረ ዳዊት 34 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 34:11-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos