መዝሙር 24:1-4
መዝሙር 24:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ። አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ። አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና። በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ። አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
ያጋሩ
መዝሙር 24 ያንብቡመዝሙር 24:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤ በውሆችም ላይ አጽንቷታል። ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል? ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤ በውሸት የማይምል።
ያጋሩ
መዝሙር 24 ያንብቡመዝሙር 24:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው። ምድርን በባሕር ላይ የመሠረተው፥ ከውሃ በላይም ያጸናው እርሱ ነው። ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል። ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።
ያጋሩ
መዝሙር 24 ያንብቡ