መዝሙረ ዳዊት 24:1-4

መዝሙረ ዳዊት 24:1-4 መቅካእኤ

ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ። እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና። ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ በሽንገላ ያልማለ።