መዝ​ሙረ ዳዊት 24:1-4

መዝ​ሙረ ዳዊት 24:1-4 አማ2000

አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ። አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ፈር፤ ጠላ​ቶቼ በእኔ አይ​ሣ​ቁ​ብኝ። አን​ተን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ አያ​ፍ​ሩ​ምና። በከ​ንቱ የሚ​በ​ድሉ ሁሉ ዘወ​ትር ይፈሩ። አቤቱ፥ መን​ገ​ድ​ህን አመ​ል​ክ​ተኝ፤ ፍለ​ጋ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።