መዝሙር 17:1-5
መዝሙር 17:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ። ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ። ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም። ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ። አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
መዝሙር 17:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ። እግዚአብሔር ኀይሌ፥ አምባዬ፥ መድኀኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬም ነው። እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ። የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዐመፅ ፈሳሽም አወከኝ፤ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
መዝሙር 17:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ። ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ። ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም። ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ። አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
መዝሙር 17:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ። ዐይኖችህ እውነትን ማየት ስለሚችሉ አንተ ብቻ ልትፈርድልኝ ትችላለህ። ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም። የሰዎችን ሥራ በሚመለከት፥ አንተ በተናገርከው ቃል መሠረት፥ እኔ ከዐመፀኞች አካሄድ ራሴን ጠብቄአለሁ። ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።