እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ። ዐይኖችህ እውነትን ማየት ስለሚችሉ አንተ ብቻ ልትፈርድልኝ ትችላለህ። ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም። የሰዎችን ሥራ በሚመለከት፥ አንተ በተናገርከው ቃል መሠረት፥ እኔ ከዐመፀኞች አካሄድ ራሴን ጠብቄአለሁ። ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
መጽሐፈ መዝሙር 17 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 17:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች