መዝሙረ ዳዊት 17:1-5

መዝሙረ ዳዊት 17:1-5 መቅካእኤ

አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ተንኰል ከሌለበት ከንፈር የሚወጣውንም ጸሎቴን አድምጥ። ፍርዴ ከፊትህ ይውጣ፥ ዐይኖችህም በቅንነት ይዩ። ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፥ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ። እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።