መዝሙር 109:1-13
መዝሙር 109:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የምስጋናዬ ምንጭ የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤ ክፉዎችና አታላዮች፣ አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤ በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል። በጥላቻ ቃል ከብበውኛል፤ ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል። ስወድዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን እጸልያለሁ። በበጎ ፈንታ ክፋትን፣ በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል። ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ ከሳሽም በቀኙ ይቁም። ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት። ዕድሜው ይጠር፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው። ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ ሚስቱም መበለት ትሁን። ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ። ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤ የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት። ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር። ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

መዝሙር 109:1-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የማመሰግንህ አምላክ ሆይ፥ እባክህ ዝም አትበል። ክፉዎችና ሐሰተኞች ተቃውመውኛል፤ በእኔ ላይ በሐሰት ይናገራሉ። በጥላቻ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ያለ ምክንያትም አደጋ ጣሉብኝ ለወዳጅነቴ የመለሱልኝ አጸፋ ክስ ነው፤ እኔ ግን እጸልይላቸዋለሁ። በመልካም ፈንታ ክፉ፥ በፍቅር ፈንታ ጥላቻ ይመልሱልኛል። በእርሱ ላይ የሚፈርድ ዐመፀኛ ዳኛ ሠይም አንዱም ሰው እንዲከስሰው አድርግ፤ በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይመለስ፤ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቈጠርበት፤ ዕድሜውም በቶሎ ይቀጭ፤ ሥራውንም ሌላ ሰው ይውሰድበት። ልጆቹ ያለ አባት ይቅሩ፤ ሚስቱም ባልዋ የሞተባት ሴት ትሁን። ልጆቹ ቤት የሌላቸው ለማኞች ይሁኑ፤ አሁን ከሚኖሩበት ፍርስራሽ ቤት እንኳ ይባረሩ። ንብረቱ ሁሉ በዕዳ ይያዝበት፤ ለፍቶ ያገኘውን ጥሪት ሁሉ ባዕዳን ሰዎች ይውሰዱበት። የሚራራለት ሰው ከቶ አይኑር፤ ድኻ ዐደግ ልጆቹን የሚንከባከባቸው ሰው አይገኝ። ለስሙ መጠሪያ የሚሆን አንድ ልጅ እንኳ አይቅርለት፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚያስታውሰው አይኑር።
መዝሙር 109:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አምላክ ሆይ፥ ምስጋናዬን ዝም አትበል፥ የክፉና የተንኰለኛ አፎች በላዬ ተላቅቀውብኛልና፥ በሐሰት አንደበትም በላዬ ተናገሩ፥ በጥላቻ ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም አጠቁኝ። በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ። በመልካም ፋንታ ክፉን፥ በፍቅር ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ። በላዩ ክፉ ሰውን ሹም፥ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም። በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፥ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት። ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፥ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ። ልጆቹም ያለ አባት ይቅሩ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን። ልጆቹም እጅጉን ይቅበዝበዙ፥ ይለምኑም፥ ከፈራረሱ ቤቶቻቸውም ሳይቀር ይባረሩ። ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት። በቸርነት የሚያግዘውንም አያግኝ፥ ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር። ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።