መዝሙረ ዳዊት 109:1-13

መዝሙረ ዳዊት 109:1-13 መቅካእኤ

አምላክ ሆይ፥ ምስጋናዬን ዝም አትበል፥ የክፉና የተንኰለኛ አፎች በላዬ ተላቅቀውብኛልና፥ በሐሰት አንደበትም በላዬ ተናገሩ፥ በጥላቻ ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም አጠቁኝ። በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ። በመልካም ፋንታ ክፉን፥ በፍቅር ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ። በላዩ ክፉ ሰውን ሹም፥ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም። በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፥ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት። ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፥ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ። ልጆቹም ያለ አባት ይቅሩ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን። ልጆቹም እጅጉን ይቅበዝበዙ፥ ይለምኑም፥ ከፈራረሱ ቤቶቻቸውም ሳይቀር ይባረሩ። ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት። በቸርነት የሚያግዘውንም አያግኝ፥ ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር። ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።