የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 109

109
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
አምላክ ሆይ፥ ምስጋናዬን ዝም አትበል፥
2 # መዝ. 35፥22፤ 83፥1። የክፉና የተንኰለኛ አፎች በላዬ ተላቅቀውብኛልና፥
በሐሰት አንደበትም በላዬ ተናገሩ፥
3በጥላቻ ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም አጠቁኝ።
4በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
5 # መዝ. 35፥12፤ 38፥21፤ ምሳ. 17፥13፤ ኤር. 18፥20። በመልካም ፋንታ ክፉን፥
በፍቅር ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።
6በላዩ ክፉ ሰውን ሹም፥
ሰይጣንም#109፥6 ከሳሽም በቀኙ ይቁም።
7በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፥
ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።
8 # የሐዋ. 1፥20። ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፥
ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።
9 # ዘፀ. 22፥23፤ ኤር. 18፥21። ልጆቹም ያለ አባት ይቅሩ፥
ሚስቱም መበለት ትሁን።
10ልጆቹም እጅጉን ይቅበዝበዙ፥ ይለምኑም፥
ከፈራረሱ ቤቶቻቸውም ሳይቀር ይባረሩ።
11ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥
እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።
12በቸርነት የሚያግዘውንም አያግኝ፥
ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
13 # መዝ. 21፥11፤ ምሳ. 10፥7። ተተኪ አይኑረው፥
በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።
14 # ዘፀ. 20፥5። የአባቶቹ ጥፋት በጌታ ፊት ትታወስ፥
የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።
15 # መዝ. 34፥16፤ 90፥8። በጌታ ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፥
መታሰቢያቸውም ከምድረ ገጽ ይጥፋ።
16በቸርነት ለመመላለስ አላሰበምና፥
ችግረኛንና ምስኪንን
ልቡ የተሰበረውንም ለመግደል ያሳድድ ነበር።
17መራገምን ወደደ፥ ወደ እርሱም መጣች፥
በረከትንም አልመረጠም፥ ከእርሱም ራቀች።
18መራገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥
እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥
እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።
19እንደሚለብሰው ልብስ፥
ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ትሁነው።
20ይህ ቅጣት በሚከሱኝና
በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ላይ ከጌታ ዘንድ ይሁን።
21አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ስትል ታደገኝ፥
ጽኑ ፍቅርህ መልካም ናትና አድነኝ።
22እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥
በውስጤም ልቤ ቆስሎአል።
23እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥
እንደ አንበጣም እረገፍሁ።
24 # መዝ. 69፥11-13። ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ፥
ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
25እኔም በእነርሱ ዘንድ መሳለቂያ ሆንሁ፥
ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።
26አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥
እንደ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ።
27አቤቱ፥ እጅህ ይህች መሆኗን፥
አንተም ይህንን እንዳደረግህ ይወቁ።
28እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ትባርካለህ፥
በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥
አገልጋይህ ግን ደስ ይበለው።
29የሚከሱኝ እፍረትን ይልበሱ፥
እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።
30 # መዝ. 111፥1። ጌታን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ።
በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፥
31ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ
ከድሀ በኩል ቆሞአልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ