የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 110

110
1የዳዊት መዝሙር።
# ማቴ. 22፥44፤ የሐዋ. 2፥34-35፤ 1ቆሮ. 15፥25፤ ዕብ. 1፥13፤ 8፥1፤ 10፥12-13፤ 1ጴጥ. 3፥22። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”
2ጌታ የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፥
በጠላቶችህም መካከል ግዛ።
3 # መዝ. 2፥7፤ 89፥27፤ ኢሳ. 49፥1። ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥
የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥
የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።
4 # መዝ. 89፥35፤ 132፥11፤ ዘፍ. 14፥18፤ ዕብ. 5፥6፤ 7፥21። “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት
አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ”፥
ጌታ ማለ፥ አይጸጸትምም።
5 # መዝ. 2፥9፤ ራእ. 2፥27፤ 12፥5፤ 19፥15። ጌታ በቀኝህ፥
ነገሥታትን በቁጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።
6በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥
ሬሳዎችንም ይከምራል፥
በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል።
7 # መዝ. 3፥4። በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ይጠጣል፥
ከዚህም የተነሣ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ