የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 111

111
1 # መዝ. 138፥1። ሃሌ ሉያ!
በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም
ጌታን በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
2የጌታ ሥራዎች ታላላቅ ናቸው፥
ደስ በሚሰኙባቸው ሁሉ ይፈለጋሉ።
3ሥራው ምስጋናና ግርማ ነው፥
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4 # መዝ. 103፥8፤ 112፥4። ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፥
ጌታ መሓሪና ርኅሩኅ ነው።
5ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፥
ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል።
6የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ
ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።
7የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ናቸው፥
ትእዛዛቱም በሙሉ የታመኑ ናቸው፥
8ለሁልጊዜና ዘለዓለምም የጸኑ ናቸው፥
በእውነትና በጽድቅም የተሠሩ ናቸው።
9ለሕዝቡ መዳንን ላከ፥
ኪዳኑንም ለዘለዓለም ደነገገ፥
ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10 # ምሳ. 1፥7፤ 9፥10፤ ሲራ. 1፥16። የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥
የሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋልን ያገኛሉ፥
ውዳሴውም ለዘለዓለም ይኖራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ