የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 108

108
1የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
2 # መዝ. 57፥8-12። አምላኬ ሆይ ልቤ ጽኑ ነው፥
እቀኛለሁ፥ በክብሬም እዘምራለሁ።
3 # ኢዮብ 38፥12። በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እንዲሁ፥
እኔም ማለዳን ልቀስቅሰው።
4 # መዝ. 9፥12፤ 18፥50፤ 148፥13። አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፥
በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ፥
5 # መዝ. 36፥6፤ 71፥19። ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥
እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና።
6አቤቱ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
7ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፥
በቀኝህ አድን አድምጠኝም።
8 # መዝ. 60፥8-14። እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፦
“ደስ እያለኝ ሴኬምንም እከፋፍላለሁ፥
የሱኮትንም ሸለቆ እሰፍራለሁ።
9ገለዓድ የእኔ ነው ምናሴም የእኔ ነው፥
ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቁር ነው።
ይሁዳ በትረ መንግሥቴ፥
10 # ሩት 4፥7-8። ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥
በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፥
በፍልስጥኤም ላይ ድሌን ዐውጃለሁ።
11ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶምያስ ድረስስ ማን ይመራኛል?
12 # መዝ. 44፥10። አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር መውጣት አቆምህ።
13በጥቃታችን ድረስልን፥
የሰውም ማዳን ከንቱ ነው።
14በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን፥
እርሱም የሚያስጨንቁንን ይረጋግጣቸዋል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ