የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 106:16-33

መዝሙር 106:16-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና። ከበ​ደ​ላ​ቸው ጎዳና ተቀ​በ​ላ​ቸው፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ተሠ​ቃ​ይ​ተ​ዋ​ልና። ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም መብ​ልን ሁሉ ተጸ​የ​ፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተ​ጨ​ነ​ቁም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። ቃሉን ልኮ ፈወ​ሳ​ቸው፥ ከጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትም ይሠ​ዉ​ለት፥ በደ​ስ​ታም ሥራ​ውን ይን​ገሩ። በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥ እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በጥ​ል​ቅም ያለ​ች​ውን ድን​ቁን ዐወቁ። ተና​ገረ፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ተነሣ፥ ሞገ​ድም ከፍ ከፍ አለ። ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች። ደነ​ገጡ፥ እንደ ሰካ​ራ​ምም ተን​ገ​ዳ​ገዱ፥ ጥበ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ተዋጠ። በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። ዐውሎ ነፋ​ሱ​ንም ጸጥ አደ​ረገ፥ ባሕ​ሩም ዝም አለ። ማዕ​በ​ሉም ዝም አለ፥ አር​ፈ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው። ወደ ፈለ​ጉ​ትም ወደብ መራ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረ​ቱን ለሰው ልጆ​ችም ድን​ቁን ንገሩ። በአ​ሕ​ዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል። ወን​ዞ​ችን ምድረ በዳ አደ​ረገ፥ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ደረቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤

መዝሙር 106:16-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ። በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤ እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ። ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር። ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም። በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጕረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም። በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤ ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ። ራሳቸውን ከበኣል ፌጎር ጋራ አቈራኙ፤ ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤ በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ መቅሠፍትም በላያቸው መጣ። ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፤ ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት። ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤ የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።

መዝሙር 106:16-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በበረሓ ሰፍረው ሳሉ በሙሴና የእግዚአብሔር ቅዱስ አገልጋይ በሆነው በአሮን ቀኑባቸው። ምድርም ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ አቤሮንንና ቤተሰቡንም ከደነቻቸው። በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ። በኮሬብ ሳሉ የወርቅ ጥጃ ሠሩ፤ ለዚያም ጣዖት ሰገዱ። የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ። በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ። በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ። በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስላልተማመኑ መልካሚቷን ምድር ናቁ። በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው አጒረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንሰማም አሉ። ስለዚህ እጁን አንሥቶ በመማል በበረሓ የሚያጠፋቸው መሆኑን ነገራቸው፤ ዘሮቻቸውን ሁሉ በአሕዛብ መካከል እንደሚጥላቸውና በመላው ዓለም እንደሚበታትናቸው ገለጠላቸው። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ በፔዖር የነበረውን ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ጣዖት አመለኩ፤ ሕይወት ለሌላቸው አማልክት የቀረበውንም የመሥዋዕት ሥጋ በሉ። በክፉ ሥራቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በዚህ ምክንያት መቅሠፍት በመካከላቸው ተነሣ። ነገር ግን ፊንሐስ ተነሥቶ በደል የፈጸሙትን በቀጣቸው ጊዜ መቅሠፍቱ ተወገደ። ይህም አድራጎቱ ወደ ፊት ለሚከተለው ትውልድ ለዘለዓለም እንደ መልካም ሥራ ሆኖ ተቈጠረለት። በመሪባ ምንጮች አጠገብ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በእነርሱም ምክንያት ሙሴ ችግር ላይ ወደቀ። እጅግ አስመርረውት ስለ ነበር ሙሴ ራሱን ባለመቈጣጠር ተናገረ።

መዝሙር 106:16-33 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሙሴንም፥ ጌታ የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው። ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥ በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባም ክፉዎችን አቃጠላቸው። በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ። ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በቀይ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ። እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ። የምትወደደውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥ በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፥ የጌታን ቃል አልሰሙም። በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው። ከባዓል ፔዖርም ጋር ተጣበቁ፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ፥ በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ። ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፥ ያም እስከ ዘለዓለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት። በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፥ በእነርሱም የተነሣ ሙሴ ተበሳጨ፥ በከንፈሮቹም ያለማስተዋል ተናገረ።