የናሱን ደጆች ሰብሮአልና፥ የብረቱንም መወርወሪያ ቀጥቅጦአልና። ከበደላቸው ጎዳና ተቀበላቸው፥ በኀጢአታቸው ተሠቃይተዋልና። ሰውነታቸውም መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተጨነቁም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሰው ልጆችም ያደረገውን ድንቁን ንገሩ፤ የምስጋና መሥዋዕትም ይሠዉለት፥ በደስታም ሥራውን ይንገሩ። በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራቸውን የሚሠሩ፥ እነርሱ የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በጥልቅም ያለችውን ድንቁን ዐወቁ። ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥ ሞገድም ከፍ ከፍ አለ። ወደ ሰማይ ይወጣሉ፥ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፤ ሰውነታቸውም በመከራ ቀለጠች። ደነገጡ፥ እንደ ሰካራምም ተንገዳገዱ፥ ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠ። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። ዐውሎ ነፋሱንም ጸጥ አደረገ፥ ባሕሩም ዝም አለ። ማዕበሉም ዝም አለ፥ አርፈዋልና ደስ አላቸው። ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው። የእግዚአብሔርን ምሕረቱን ለሰው ልጆችም ድንቁን ንገሩ። በአሕዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደርጉታል፥ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያመሰግኑታል። ወንዞችን ምድረ በዳ አደረገ፥ የውኃውንም ምንጮች ደረቅ አደረጋቸው፤
መዝሙረ ዳዊት 106 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 106:16-33
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች