የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 106:16-33

መዝሙር 106:16-33 NASV

በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ። በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤ እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ። ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር። ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም። በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጕረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም። በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤ ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ። ራሳቸውን ከበኣል ፌጎር ጋራ አቈራኙ፤ ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤ በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ መቅሠፍትም በላያቸው መጣ። ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፤ ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት። ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤ የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።