መዝሙር 101:1-4
መዝሙር 101:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ። እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ፣ በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ። በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም። ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።
መዝሙር 101:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ ፊትህ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ አልቋልና፥ አጥንቶቼም እንደ ሣር ደርቀዋልና። ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። እህል መብላት ተረስቶኛልና