መዝሙረ ዳዊት 101:1-4

መዝሙረ ዳዊት 101:1-4 መቅካእኤ

አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ። ነቀፋ በሌለበት መንገድን እጓዛለሁ፥ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ። በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥ ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ። ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥ ክፉን አላውቀውም።