መጽሐፈ መዝሙር 101:1-4

መጽሐፈ መዝሙር 101:1-4 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም። ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? ከቤተሰቤ ጋር በቅንነት እኖራለሁ። ክፉ ነገር ሲደረግ አይቼ ዝም አልልም፤ ከእግዚአብሔር የራቁ ሰዎች የሚያደርጉትን ሁሉ እጠላለሁ፤ ከቶም አልተባበራቸውም። ጠማማ ልብ ያላቸው ሰዎች ከእኔ ይራቁ፤ ከክፋትም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም።