መዝሙር 100:2-4
መዝሙር 100:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ። በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን አላኖርሁም፤ ዐመፃ የሚያደርጉትን ጠላሁ። ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም።
መዝሙር 100:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ። እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የርሱ ነን፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን። በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
መዝሙር 100:2-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት! የደስታ መዝሙር እየዘመራችሁ ወደ እርሱ ፊት ቅረቡ! እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን። እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።