ምሳሌ 27:17-21
ምሳሌ 27:17-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል። በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል። ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣ የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል። ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣ የሰውም ዐይን አይረካም። ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣ ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።
Share
ምሳሌ 27 ያንብቡምሳሌ 27:17-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ብረት ብረትን እንደሚስል ሰውም እርስ በእርሱ አንዱ ከሌላው ይማራል። የበለስን ዛፍ ተንከባክበህ ብትጠብቅ የበለስ ፍሬ ትበላለህ፤ አሳዳሪውን የሚንከባከብ አገልጋይም ይከበራል። ውሃ እንደ መስተዋት ሆኖ ፊትህን እንደሚያሳይህ ኅሊናህም እንደ መስተዋት ሆኖ የራስህን ጠባይ መልሶ ያሳይሃል። ሞትና መቃብር በቃን እንደማይሉ፥ የሰው ምኞትም እንደዚሁ ነው። ወርቅና ብር በእሳት ተፈትነው ጥራታቸው እንደሚታወቅ፥ የሰውም መልካምነት የሚቀርብለትን ምስጋና በሚቀበልበት ሁኔታ ተፈትኖ ይታወቃል።
Share
ምሳሌ 27 ያንብቡ