የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 27

27
1ጊዜ የሚያመጣውን ነገር ስለማታውቅ ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ። #ያዕ. 4፥13-16።
2ሌሎች ሰዎች ያመስግኑህ እንጂ ራስህን አታመስግን፤ ሰዎች ስለ አንተ ይመስክሩ እንጂ፥ አንተ ስለ ራስህ መልካምነት አትናገር።
3ድንጋይና አሸዋ ከባድ ናቸው፤ ሞኝ ሰው የሚያነሣሣው ቊጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
4ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው።
5በግልጽ የሚነገር ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
6የወዳጅ ማቊሰል ለመልካም ነገር ነው፤ የጠላት መሳም ግን ለጥፋት ነው።
7የጠገበ ሰው ማር. አይጥመውም፤ የራበው ሰው ግን መራራው ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል።
8ከቤቱ ርቆ የሚሄድ ሰው ከጎጆዋ ርቃ እንደምትበር ወፍ ተንከራታች ይሆናል።
9ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።
10ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
11ልጄ ሆይ! ጠቢብ ብትሆን ደስ ይለኛል፤ ለሚሰድበኝ ሁሉ የምሰጠውም መልስ ይኖረኛል።
12ብልኅ ሰው መከራ ሲመጣ አይቶ ይሸሻል፤ ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ ከገባ በኋላ እንደገና ይጸጸታል።
13ማንም ሰው ለእንግዳ ሰው ከተዋሰ ልብሱን ውሰድ፤ ለማይታወቅ ሰው መያዣ እንዲሆን አንተ ዘንድ አስቀምጠው።
14ጠዋት በማለዳ ከፍ ባለ ድምፅ ለጐረቤት ሰላምታ መስጠት እንደ መራገም ይቈጠራል።
15ተጨቃጫቂ ሚስት እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት፤ 16ነፋስን ለማቆም ዘይትንም በእጅ ጨብጦ ለመያዝ እንደማይቻል ሁሉ እርስዋንም ዝም ማሰኘት አይቻልም። 17ብረት ብረትን እንደሚስል ሰውም እርስ በእርሱ አንዱ ከሌላው ይማራል።
18የበለስን ዛፍ ተንከባክበህ ብትጠብቅ የበለስ ፍሬ ትበላለህ፤ አሳዳሪውን የሚንከባከብ አገልጋይም ይከበራል።
19ውሃ እንደ መስተዋት ሆኖ ፊትህን እንደሚያሳይህ ኅሊናህም እንደ መስተዋት ሆኖ የራስህን ጠባይ መልሶ ያሳይሃል።
20ሞትና መቃብር በቃን እንደማይሉ፥ የሰው ምኞትም እንደዚሁ ነው።
21ወርቅና ብር በእሳት ተፈትነው ጥራታቸው እንደሚታወቅ፥ የሰውም መልካምነት የሚቀርብለትን ምስጋና በሚቀበልበት ሁኔታ ተፈትኖ ይታወቃል።
22እህል በሙቀጫ ውስጥ በዘነዘና እንደሚወቀጥ ሞኝንም ለመሞት እስኪቃረብ ድረስ ብትመታው እንኳ ሞኝነቱን ከእርሱ ማስወገድ አትችልም።
23በጎችህን ጠንቅቀህ ዕወቅ፤ ለከብቶችህም ጥንቃቄ አድርግ። 24ሀብት ለዘወትር የሚኖር አይደለም፤ መንግሥታትም ቢሆኑ ዘለዓለም አይኖሩም። 25ደረቅ ሣር ታጭዶ አዲስ ሣር ሲበቅል፥ በተራራ ላይ ያለው ሣርም ሲሰበሰብ፥ 26በጎችህ ለልብስ የሚሆን ጠጒር ይሰጡሃል፤ ከፍየሎችህ ጥቂቶቹን በመሸጥ የመሬት መግዣ ገንዘብ ታገኛለህ። 27የቀሩት ፍየሎች ለአንተና ለቤተሰብህ ለሴት አገልጋዮችህም ጭምር የሚጠቅም ወተት ይሰጡሃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}