ምሳሌ 20:22-30
ምሳሌ 20:22-30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል። ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም። የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል? በችኰላ ስእለት መሳል፣ ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው። ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤ የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል። የሰው መንፈስ ለእግዚአብሔር መብራት ነው፤ ውስጣዊ ማንነቱንም ይፈትሻል። ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል። የጕልማሶች ክብር ብርታታቸው፣ የሽማግሌዎችም ሞገስ ሽበታቸው ነው። የሚያቈስል በትር ክፋትን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የውስጥ ሰውነትን ያጠራል።
ምሳሌ 20:22-30 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን። ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም። የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቃናል፤ ሟች ግን መንገዱን እንዴት ያውቃል? ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል። ብልህ ንጉሥ የኃጥኣን መንሽ ነው፥ በእነርሱ ላይም መንኰራኵርን ይነዳባቸዋል። የሰው መንፈስ የሆድን መዛግብት የሚመረምር፥ የእግዚአብሔር መብራት ነው። ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑንም በእውነት ይከቡታል። ለጐልማሶች ጌጣቸው ጥበብ ነው። ለሽማግሌዎችም ክብራቸው ሽበት ነው። ሽብርና ስደት ክፉዎችን ድንገት ይገናኛቸዋል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ዕቃ ይገባል።
ምሳሌ 20:22-30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል። ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም። የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል? በችኰላ ስእለት መሳል፣ ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው። ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤ የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል። የሰው መንፈስ ለእግዚአብሔር መብራት ነው፤ ውስጣዊ ማንነቱንም ይፈትሻል። ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል። የጕልማሶች ክብር ብርታታቸው፣ የሽማግሌዎችም ሞገስ ሽበታቸው ነው። የሚያቈስል በትር ክፋትን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የውስጥ ሰውነትን ያጠራል።
ምሳሌ 20:22-30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ክፉ ያደረገብህን ሰው አንተም መልሰህ ክፉ አታድርግበት፤ በእግዚአብሔር ታመን፤ እርሱም ይታደግሃል። እግዚአብሔር ያልተስተካከለ መስፈሪያና ሐሰተኛ ሚዛን ይጸየፋል። እግዚአብሔር የምንራመድበትን መንገድ ወስኖአል፤ ታዲያ፥ ሰው ሕይወቱ ወዴት አቅጣጫ እንደሚያመራ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? በኋላ እንዳትጸጸት ለእግዚአብሔር ከመሳልህ በፊት ተጠንቅቀህ አስብ። ብልኅ ንጉሥ ዐመፀኞችን ለይቶ ያውቃቸዋል፤ ያለ ምሕረትም ይቀጣቸዋል። የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ስለ ሆነ የሰውን ውስጣዊ ሰውነት ሁሉ ይመረምራል። ቸርነትና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ መንግሥቱም በእውነተኛነት ላይ ጸንቶ ይኖራል። የወጣቶች መመኪያ ብርታታቸው ነው፤ የሽማግሌዎችም መከበሪያ ሽበታቸው ነው። የሚያቈስል ቅጣት ክፉ ነገርን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የሰውን ውስጣዊ ሁኔታ ያነጻል።
ምሳሌ 20:22-30 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ክፉ እመልሳለሁ አትበል፥ ጌታን ተማመን፥ እርሱም ያድንሃል። ሁለት ዓይነት ሚዛን በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም። የሰው አካሄዱ ከጌታ ዘንድ ነው፥ እንግዲስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል? ሰው በችኰላ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው። ጠቢብ ንጉሥ ኀጥኣንን በመንሽ ይበትናቸዋል፥ መንኰራኵሩንም በእነርሱ ላይ ያንኰራኩርባቸዋል። የሰው መንፈስ የጌታ መብራት ነው የሆዱን ጉርጆች ሁሉ የሚመረምር። ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል፥ ዙፋኑም በቸርነት ይበረታል። የጎበዛዝት ክብር ጉልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው። የሰንበር ቁስል ክፉዎችን ያነጻል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ጉርጆች ይገባል።