የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍልቍ 2:10-34

ዘኍልቍ 2:10-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“በአ​ዜብ በኩል በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የሮ​ቤል ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የሮ​ቤ​ልም ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የስ​ም​ዖን ነገድ ናቸው፤ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አለቃ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋ​ድም ልጆች አለቃ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤል​ሳፍ ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበሩ። ከሮ​ቤል ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ቀጥ​ለው ይጓ​ዛሉ። “ከዚ​ያም በኋላ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ በሰ​ፈ​ሮ​ቹም መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ይጓ​ዛል፤ እንደ አሰ​ፋ​ፈ​ራ​ቸው ሰው ሁሉ በየ​ስ​ፍ​ራው፥ በየ​ዓ​ላ​ማ​ውም ይጓ​ዛሉ። “በባ​ሕር በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሜ​ሁድ ልጅ ኤሌ​ሳማ ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የም​ናሴ ነገድ ይሆ​ናል፤ የም​ና​ሴም ልጆች አለቃ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የብ​ን​ያም ነገድ ይሆ​ናል፤ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች አለቃ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም፥ ሠላሳ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከኤ​ፍ​ሬም ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ስም​ንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሦስ​ተኛ ሆነው ይጓ​ዛሉ። “በመ​ስዕ በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የዳ​ንም ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዜር ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የአ​ሴር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የአ​ሴ​ርም ልጆች አለቃ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋጋ​ኤል ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አንድ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ ይሆ​ናል፤ የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች አለቃ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከዳን ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም በየ​ዓ​ላ​ማ​ቸው በመ​ጨ​ረሻ ይጓ​ዛሉ።” ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ እነ​ዚህ ናቸው፤ ከየ​ሰ​ፈሩ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ። ሌዋ​ው​ያን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ በየ​ዓ​ላ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ሰፈሩ፤ እን​ዲ​ሁም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ተጓዙ።

ዘኍልቍ 2:10-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በደቡብ በኩል፤ የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነው። ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ ዘጠኝ ሺሕ ሦስት መቶ ነው። ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት አርባ ዐምስት ሺሕ ስድስት መቶ ዐምሳ ነው። በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ዐምሳ አንድ ሺሕ አራት መቶ ዐምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ። ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ። በምዕራብ በኩል፤ የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት አርባ ሺሕ ዐምስት መቶ ነው። ከእነዚህም የምናሴ ነገድ ይቀጥላል፣ የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነው። ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፣ የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ ነው። በየሰራዊታቸው ሆነው ከኤፍሬም ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ስምንት ሺሕ አንድ መቶ ናቸው፤ እነዚህ ሦስተኛ ሆነው ይመጣሉ። በሰሜን በኩል፤ የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ስድሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነው። የአሴር ነገድ ከእነዚህ ቀጥሎ ይሰፍራል፤ የአሴር ሕዝብ አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት አርባ አንድ ሺሕ ዐምስት መቶ ነው። ከዚያም የንፍታሌም ነገድ ይቀጥላል፤ የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነው። በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ ዐምሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ። በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ናቸው፤ ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ አልተቈጠሩም። ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።

ዘኍልቍ 2:10-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በደቡብ በኩል በየሠራዊቶቻቸው የሮቤል ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የሮቤልም ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የስምዖን ነገድ ናቸው፤ የስምዖንም ልጆች አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋድም ልጆች አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነበሩ። ከሮቤል ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነርሱም ቀጥለው ይጓዛሉ። ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ። በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ይሆናል፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የብንያም ነገድ ይሆናል፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ። በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የአሴር ነገድ ይሆናሉ፤ የአሴርም ልጆች አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የንፍታሌም ነገድ ይሆናል፤ የንፍታሌምምም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ። ከእስራኤል ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ እነዚህ ናቸው፤ ከየሰፈሩ በየሠራዊቶቻቸው የተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።

ዘኍልቍ 2:10-34 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በስተ ደቡብ በኩል በሮቤል ክፍል ዓርማ ሥር በየቡድናቸው ይሰፍራሉ፤ የሮቤል ነገድ መሪ የሸዴኡር ልጅ ኤሊጹር ነው፤ የእነርሱም ብዛት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበር። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የስምዖን ልጆች ይሆናሉ፤ የስምዖን ነገድ መሪ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ነው፤ የእነርሱም ብዛት ኀምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበር። ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ነገድ መሪ የደዑኤል ልጅ ኤልያሳፍ ነው፤ የእነርሱም ብዛት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ኀምሳ ነበር። እንደየክፍላቸው በሮቤል ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ኀምሳ ነበር። በዚህ ዐይነት የሮቤል ክፍል ሁለተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎችና በመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎች መካከል ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን ይዘው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዱም ክፍል ሰፈሩ ተለይቶ በሚታወቅበት ዓርማ ሥር ምድብ ተራውን ጠብቆ ይጓዛል። በስተምዕራብ በኩል በኤፍሬም ክፍል ዓርማ ሥር በየቡድናቸው ይሰፍራሉ፤ የኤፍሬም ነገድ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሻማዕ ነው፤ የእነርሱም ብዛት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበር። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የምናሴ ልጆች ይሆናሉ፤ የምናሴ ነገድ መሪ የጴዳጹር ልጅ ገማልኤል ነው፤ የእነርሱም ብዛት ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበር፤ ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፤ የብንያም ነገድ መሪ የጊድዖን ልጅ አቢዳን ነበር፤ የእነርሱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበር። እንደየክፍላቸው በኤፍሬም ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የኤፍሬም ክፍል ሦስተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል። በስተ ሰሜን በኩል በዳን ክፍል ዓርማ ሥር የሚሰፍሩ ወገኖች ናቸው፤ የዳን ነገድ መሪ የዓሚሻዳይ ልጅ አሒዔዜር ነው፤ ብዛታቸውም ሥልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበር። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የአሴር ልጆች ይሆናሉ፤ የአሴር ነገድ መሪ የዖክሪን ልጅ ፋግዒኤል ነው፤ የእነርሱም ብዛት አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበር። ከዚያም የንፍታሌም ነገድ ይቀጥላል፤ የንፍታሌም ነገድ መሪ የዔናን ልጅ አሒራዕ ነው፤ የእነርሱም ብዛት ኃምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበር። እንደየክፍላቸው በዳን ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የዳን ክፍል የመጨረሻ ተራ ተጓዥ ይሆናል። እስራኤላውያን በየነገዳቸውና በየክፍላቸው የተቈጠሩት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበር። ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ከሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ ጋር አልተቈጠሩም። በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤ እያንዳንዱ ነገድ ዓርማውን በመከተል ይሰፍር ነበር፤ እያንዳንዱም በየቤተሰቡ ተመድቦ ይጓዝ ነበር።

ዘኍልቍ 2:10-34 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“በደቡብ በኩል በየሠራዊቶቻቸው የሮቤል ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የሮቤልም ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የስምዖን ነገድ ናቸው፤ የስምዖንም ልጆች አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ኀምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋድም ልጆች አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ኀምሳ ነበሩ። ከሮቤል ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ኀምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ኀምሳ ነበሩ። እነርሱም ቀጥለው ይጓዛሉ። “ከዚያም በኋላ በሰፈሮቹም መካከል የመገናኛው ድንኳን ከሌዋውያን ሰፈር ጋር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው እያንዳንዱ ሰው ስፍራቸውን ይዘው በየዓላሞቻቸው ይጓዛሉ። “በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ነበረ፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የብንያም ነገድ ነበረ፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ። “በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ስልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የአሴር ነገድ ይሆናሉ፤ የአሴርም ልጆች አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የንፍታሌም ነገድ ነበረ፤ የንፍታሌምም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።” ከእስራኤል ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ እነዚህ ናቸው፤ ከየሰፈሩ በየሠራዊቶቻቸው የተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ። ሌዋውያን ግን ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች እየሆኑ ተጓዙ።