ኦሪት ዘኍልቍ 2
2
የእስራኤል ነገድ በሰፈር አመዳደብ
1እግዚአብሔርም ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 2“የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ። 3በመጀመሪያ በምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት ከሠራዊቶቻቸው ጋር የይሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። 4የተቈጠሩ ሠራዊቱም ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። 5በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮርም ልጆች አለቃ የሰገር ልጅ ናትናኤል ነበረ። 6የተቈጠሩ ሠራዊቱም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 7በእነርሱም አጠገብ የዛብሎን ነገድ ነበረ፤ የዛብሎንም ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበረ። 8የተቈጠሩ ሠራዊቱም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 9ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።
10“በአዜብ በኩል በየሠራዊቶቻቸው የሮቤል ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የሮቤልም ልጆች አለቃ የሴድዮር ልጅ ኤሊሱር ነበረ። 11የተቈጠሩ ሠራዊቱም አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። 12በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የስምዖን ነገድ ናቸው፤ የስምዖንም ልጆች አለቃ የሲሩሳዴ ልጅ ሰላምያል ነበረ። 13የተቈጠሩ ሠራዊቱም አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። 14በእነርሱም አጠገብ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋድም ልጆች አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤልሳፍ ነበረ። 15የተቈጠሩ ሠራዊቱም አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነበሩ። 16ከሮቤል ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነርሱም ቀጥለው ይጓዛሉ።
17“ከዚያም በኋላ የምስክሩ ድንኳን፥ በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ወገን ይጓዛል፤ እንደ አሰፋፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው፥ በየዓላማውም ይጓዛሉ።
18“በባሕር በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሜሁድ ልጅ ኤሌሳማ ነበረ። 19የተቈጠሩ ሠራዊቱም አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። 20በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ይሆናል፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፈዳሱር ልጅ ገማልያል ነበረ። 21የተቈጠሩ ሠራዊቱም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 22በእነርሱም አጠገብ የብንያም ነገድ ይሆናል፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። 23የተቈጠሩ ሠራዊቱም፥ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 24ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ።
25“በመስዕ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዲ ልጅ አክያዜር ነበረ። 26የተቈጠሩ ሠራዊቱም ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። 27በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የአሴር ነገድ ይሆናሉ፤ የአሴርም ልጆች አለቃ የኤክራን ልጅ ፋጋኤል ነበረ። 28የተቈጠሩ ሠራዊቱም አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። 29በእነርሱም አጠገብ የንፍታሌም ነገድ ይሆናል፤ የንፍታሌምም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበረ። 30የተቈጠሩ ሠራዊቱም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 31ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላማቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።”
32ከእስራኤል ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ እነዚህ ናቸው፤ ከየሰፈሩ በየሠራዊቶቻቸው የተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። 33ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። 34የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በየዓላማዎቻቸው ሰፈሩ፤ እንዲሁም በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ