ዘኍል 12:13-14
ዘኍል 12:13-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህም ሙሴ፣ “አምላክ (ኤል) ሆይ፤ እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጮኸ። እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት።
Share
ዘኍል 12 ያንብቡዘኍል 12:13-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ላይ ቢተፋባት እንኳ ኀፍረትዋን ተሸክማ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ትቈይ የለምን? ስለዚህም እርስዋ ከሰፈር ወጥታ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በገለልተኛ ቦታ ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሳ ወደ ሰፈር ልትገባ ትችላለች።”
Share
ዘኍል 12 ያንብቡዘኍል 12:13-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ፥ “አቤቱ፥ እባክህ፥ አድናት” አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራቁን በፊቷ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመለስ” አለው።
Share
ዘኍል 12 ያንብቡ