ኦሪት ዘኍልቊ 12
12
አሮንና ማርያም በሙሴ ላይ መቅናታቸው
1ሙሴም ኢትዮጵያይቱን በእርግጥ አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። 2እነርሱም፦ “በውኑ ጌታ የተናገረው በሙሴ በኩል ብቻ ነውን? በእኛስ በኩል ደግሞ ተናገሮ የለምን?” አሉ፤ ጌታም ሰማ። 3#ሲራ. 45፥4።ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።
4በድንገትም ጌታ ሙሴንና አሮንን ማርያምንም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ፤” ሦስቱም ወጡ። 5ጌታም በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡ። 6እርሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ፥ ቃሎቼን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ ጌታ በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ። 7#ዕብ. 3፥2።ከባርያዬ ከሙሴ ጋር ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው። 8እኔ በምሳሌ ሳይሆን እፊት ለፊት ከእርሱ ጋር በግልጥ እነጋገራለሁ፤ የጌታንም ሀልዎተ-ቅርፅ#12፥8 ቃሊመ-ቅርፅ፤ ለዘለዓለም የሚኖረውን የማይቀየረውንም የጌታን መኖርና ምንነት ያመለክታል። ይመለከታል፤ ታዲያ፥ በባርያዬ በሙሴ ላይ ለመናገር ለምን አልፈራችሁም?”
9በእርሱም ላይ የጌታ ቁጣ ነደደ፤ እርሱም ትቶአቸው ሄደ። 10ደመናውም ከድንኳኑ በተነሣ ጊዜ እነሆ፥ ማርያም በለምጽ ደዌ ተይዛ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር፤ አሮንም ወደ ማርያም ዘወር አለ፥ እነሆም፥ በለምጽ ደዌ ተይዛ ተመለከተ። 11አሮንም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ሆይ! ተሞኝተን ይህን አድርገናልና፥ ኃጢአትንም ሠርተናልና እባክህ፥ ኃጢአትን በእኛ ላይ አትቁጠርብን። 12ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ በማኅፀን እንደ ሞተ ልጅ እርሷ እባክህ፥ አትሁን።” 13ሙሴም እንዲህ ብሎ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ እባክህ፥ ፈውሳት።” 14#ዘኍ. 5፥2፤3።ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።” 15ማርያምም ከሰፈሩ ውጪ ሰባት ቀን ተዘግቶባት ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም።
16ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተጓዙ፥ በፋራንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ