ዘኍልቍ 11:1-3
ዘኍልቍ 11:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች። ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እሳቲቱም ጠፋች። ከእግዚአብሔርም ዘንድ በእነርሱ ላይ እሳት ስለ ነደደች የዚያ ስፍራ ስም “መካነ ውዕየት” ተብሎ ተጠራ።
Share
ዘኍልቍ 11 ያንብቡዘኍልቍ 11:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ስለ ደረሰባቸው ችግር በእግዚአብሔር ላይ አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ማጕረምረማቸውን በሰማ ጊዜ በጣም ተቈጣ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር እሳት በመካከላቸው ነደደች፤ ከሰፈሩም ዳርቻ ጥቂቱን በላች። ሕዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እሳቲቱም ጠፋች። ከዚህ የተነሣም የቦታው ስም፣ “ተቤራ” ተባለ፤ የእግዚአብሔር እሳት በመካከላቸው ነድዳለችና።
Share
ዘኍልቍ 11 ያንብቡዘኍልቍ 11:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች። ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እሳቲቱም ጠፋች። የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው።
Share
ዘኍልቍ 11 ያንብቡ