ነህምያ 8:10-12
ነህምያ 8:10-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው። ሌዋውያኑም በዚህ በተቀደሰ ዕለት ማዘን እንደማይገባቸው በማስረዳት የሕዝቡን ጩኸት ጸጥ አደረጉ፤ የተነበበላቸውን ቃል ትርጒም በሚገባ ተረድተው ስለ ነበር ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደው በመብላትና በመጠጣት እጅግ ተደሰቱ፤ ያላቸውንም ምግብ ከሌሎቹ ጋር አብረው ተካፈሉ፤
ነህምያ 8:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱም፥ “ሂዱ፤ የሰባውንም ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ለእነዚያም ምንም ለሌላቸው እድል ፈንታቸውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ እግዚአብሔርም ኀይላችን ነውና አትዘኑ” አላቸው። ሌዋውያንም “ቀኑ የተቀደሰ ነውና ዝም በሉ፤ አትዘኑም” እያሉ ሕዝቡን ሁሉ ጸጥ ያደርጉ ነበር። ሕዝቡም ሁሉ የተነገራቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈንታም ሊልኩ፥ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።
ነህምያ 8:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነህምያም፣ “ሂዱ፤ ጥሩ ምግብ በመብላት፣ ጣፋጩን በመጠጣት ደስ ይበላችሁ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ካላችሁ ላይ ከፍላችሁ ላኩላቸው። ይህች ቀን ለጌታችን የተቀደሰች ናት፤ የእግዚአብሔር ደስታ ብርታታችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው። ሌዋውያኑም፣ “ይህች ቀን የተቀደሰች ስለ ሆነች ዝም በሉ፤ አትዘኑም” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አረጋጉ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ የተነገራቸውን ቃል ተረድተው ስለ ነበረ፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ከምግባቸው ከፍለው ለመላክና ሐሤትም ለማድረግ ሄዱ።
ነህምያ 8:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፥ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፥ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። ሌዋውያንም፦ ቀኑ የተቀደሰ ነውና ዝም በሉ፥ አትዘኑም ብለው ሕዝቡን ሁሉ ጸጥ ያደርጉ ነበር። ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።
ነህምያ 8:10-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው። ሌዋውያኑም በዚህ በተቀደሰ ዕለት ማዘን እንደማይገባቸው በማስረዳት የሕዝቡን ጩኸት ጸጥ አደረጉ፤ የተነበበላቸውን ቃል ትርጒም በሚገባ ተረድተው ስለ ነበር ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደው በመብላትና በመጠጣት እጅግ ተደሰቱ፤ ያላቸውንም ምግብ ከሌሎቹ ጋር አብረው ተካፈሉ፤
ነህምያ 8:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው። ሌዋውያንም፦ “ቀኑ ቅዱስ ነውና ዝም በሉ፥ አትዘኑም” እያሉ ሕዝቡን ሁሉ ዝም አሰኙት። ሕዝቡም ሁሉ ሊበሉ፥ ሊጠጡ፥ ለሌላቸው ድርሻቸውን ሊልኩና ታላቅ ደስታ ሊያደርጉ ሄዱ፤ የተነገራቸውን ቃል ማስተዋል ችለው ነበርና።