የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 8:10-12

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 8:10-12 አማ2000

እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው። ሌዋ​ው​ያ​ንም “ቀኑ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ዝም በሉ፤ አት​ዘ​ኑም” እያሉ ሕዝ​ቡን ሁሉ ጸጥ ያደ​ርጉ ነበር። ሕዝ​ቡም ሁሉ የተ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ልና ሊበ​ሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈን​ታም ሊልኩ፥ ደስ​ታም ሊያ​ደ​ርጉ ሄዱ።