መጽሐፈ ነህምያ 8:10-12

መጽሐፈ ነህምያ 8:10-12 አማ54

እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፥ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፥ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። ሌዋውያንም፦ ቀኑ የተቀደሰ ነውና ዝም በሉ፥ አትዘኑም ብለው ሕዝቡን ሁሉ ጸጥ ያደርጉ ነበር። ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።