ሉቃስ 12:51-53
ሉቃስ 12:51-53 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡንም እንዲህ አላቸው፥ “ለምድር ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፤ ሰይፍንና መለያየትን ነው እንጂ። ከእንግዲህስ ወዲህ አምስት ሰዎች በአንድ ቤት ቢኖሩ ሦስቱ ከሁለቱ፥ ሁለቱም ከሦስቱ ይለያሉ፤ አባት ከልጁ፥ ልጅም ከአባቱ ይለያል፤ እናት ከልጅዋ፥ ልጅም ከእናቷ ትለያለች፤ አማት ከምራቷ፥ ምራትም ከአማቷ ትለያለች።”
ሉቃስ 12:51-53 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ ይመስላችኋል? አይደለም፤ እላችኋለሁ፤ እኔ የመጣሁት ለመለያየት ነው። ከአሁን ጀምሮ እርስ በርስ የተለያዩ በአንድ ቤተ ሰብ ውስጥ ዐምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሁለቱ በሦስቱ ላይ፣ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ። አባት በወንድ ልጁ ላይ፣ ወንድ ልጅም በአባቱ ላይ፣ እናት በሴት ልጇ ላይ፣ ሴት ልጅም በእናቷ ላይ፣ ዐማት በምራቷ ላይ፣ ምራትም በዐማቷ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።”
ሉቃስ 12:51-53 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። ከአሁን ጀምሮ በአንዲት ቤት አምስት ሰዎች ይኖራሉና፤ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ። አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በልጅዋ ላይ ልጅዋም በእናትዋ ላይ፥ አማት በምራትዋ ላይ ምራትም በአማትዋ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።
ሉቃስ 12:51-53 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኔ በምድር ላይ ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እኔስ ያመጣሁት መለያየትን እንጂ ሰላምን አይደለም እላችኋለሁ። ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ አምስት ሰዎች ይለያያሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፥ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይጣላሉ። አባት በልጁ ላይ፥ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በሴት ልጅዋ ላይ፥ ሴት ልጅም በእናትዋ ላይ፥ ዐማት በምራትዋ ላይ፥ ምራትም በዐማትዋ ላይ በመነሣት ይለያያሉ።”